በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ክልል ፓርቲዎች የምርጫ ቅሬታዎችን በህግና በሰላም እንደሚሞግቱ አስታወቁ


ባሕር ዳር
ባሕር ዳር

የ6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ውጤት የሚያከብሩና ቅሬታዎችንም በሕግ አግባብ ብቻ ለመፍታት እንደሚንቀሳቀሱ 19 የፖለቲካ ፓርቲዎችን የያዘው የአማራ ክልል የጋራ ምክርቤት አባላት ገልጸዋል። በአማራ ክልል የሰላም ጉዳይ ላይ ለመስራት ከሥምምነት ላይ መድረሳቸውንም አመልክተዋል።

በአማራ ክልል 19 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይንቀሳቀሳሉ። ፓርቲዎቹ የጋራ ምክር ቤትም አቋቁመዋል ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ደግሞ 18 ቱ ተሳትፈዋል።

በክልሉ የተካሄደው ምርጫ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች በነጻነት የተንቀሳቀሱበት እንደነበር ፓርቲዎቹ አስረድተዋል። በምርጫው ሂደት የተስተዋሉ ችግሮች ቢኖሩም በሕዝብ ተሳትፎ በሰላም መጠናቀቁንም የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋሁን አለምነው ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ውጤት በይፋ እስከሚገልጽ ድረስ በትዕግስት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠብቁ መሆኑን ገልፀው የምርጫ ውጤቱን በፀጋ እንደሚቀበሉና ያላቸውን ቅሬታም በሕግ አግባብ ብቻ ለመፍታት እንደሚንቀሳቀሱ አቶ ተስፋሁን ገልፀዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአማራ ክልል ፓርቲዎች የምርጫ ቅሬታዎችን በህግና በሰላም እንደሚሞግቱ አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:07 0:00


XS
SM
MD
LG