በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዋግ ኽምራ ዞን በድርቅ ጉዳት የሞቱ የቤት እንስሳት ከ10ሺሕ እንደበለጠ ተነገረ


በዋግ ኽምራ ዞን በድርቅ ጉዳት የሞቱ የቤት እንስሳት ከ10ሺሕ እንደበለጠ ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:15 0:00

በዋግ ኽምራ ዞን በድርቅ ጉዳት የሞቱ የቤት እንስሳት ከ10ሺሕ እንደበለጠ ተነገረ

በዐማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን የተከሠተው ድርቅ ባስከተለባቸው ጉዳት ምክንያት የሞቱት የቤት እንስሳት ብዛት ከዐሥር ሺሕ በላይ እንደደረሰ፣ የዞኑ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበርያ ጽ/ቤት ገለጸ፡፡

የጽ/ቤቱ ሓላፊ አቶ ምሕረት መላኩ፣ ዛሬ ዐርብ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ባለፈው ወር ብቻ፣ ከረኀቡ ጉዳት የተነሣ ከስድስት ሺሕ በላይ የቤት እንስሳት እንደሞቱ አስታውሰዋል፡፡ ቁጥሩ ሊጨምር የቻለው፣ ከሰብአዊ ርዳታው ጎን ለጎን የእንስሳት መኖ ርዳታንም በማሰባሰብ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ባለመሠራቱ ነው፤ ብለዋል፡፡

መንግሥት እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች፣ ርዳታውን በማሰባሰብ ላይ በትኩረት ካልሠሩ፣ የእንስሳት ጉዳት ሊባባስና ነዋሪውም ከአካባቢው ሊፈናቀል እንደሚችል፣ ሓላፊው አሳስበዋል፡፡

ሁለት የእርሻ በሬዎችን ጨምሮ ስምንት የቤት እንስሶቻቸው እንደሞቱባቸው የነገሩን፣ በሳሃላ ሰየምት ወረዳ መንደር 04 ነዋሪ አርሶ አደር ደሴ ገብሩ፣ በአካባቢው ለመኖርም ተቸግረው ለመሸሸም ዐቅም አጥተው ከረኀብ ጋራ ተፋጠው እንደሚገኙ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG