በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብድርና ቁጠባ ባሕል በአማራ


በአማራ ክልል ከግማሽ ሚሊየን በላይ ገበሬዎች የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ አገልግሎት እንደሚያገኙ ተገለፀ፡፡

ዋና ፅ/ቤቱ ባሕርዳር ላይ የሆነው የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) የገበሬዎችን አቅም ያጎለብታል የሚለውን የገንዘብ ወይም የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ተቋሙ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ገበሬዎችና ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች ብድር፣ ቁጠባ፣ የኀዋላና የጡረታ ክፍያ አገልግሎት ሥራዎችን ያከናውናል፡፡

ይህ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በሁሉም የአማራ ወረዳዎች ውስጥ ፅ/ቤቶችን ከፍቶ ከተጠቃሚዎች ጋር በቀጥታ እንደሚገናኝ፣ አዲስ አበባ ላይም በቅርቡ ፅ/ቤት መክፈቱን የተቋሙ የፋይናንስና የሰው ኃይል ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ጋሻው ወርቅነህ ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ ከበርካታ የሃገር ውስጥ የግልና የመንግሥት የገንዘብ ድርጅቶች፣ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ድጋፍ ሰጭዎች ጋር እንደሚሠራ ነው አቶ ጋሻው የገለፁት፡፡ በዚህ ተቋም እንቅስቃሴ ላይ ም/ሥ/አስኪያጁን አቶ ጋሻው ወርቅነህን ሰሎሞን አባተ አነጋግሯቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG