በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል የኮሌራ ወረርሽኝ የ90 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ተገለጸ


በዐማራ ክልል የኮሌራ ወረርሽኝ የ90 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:31 0:00

በዐማራ ክልል የኮሌራ ወረርሽኝ የ90 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ተገለጸ

በዐማራ ክልል፣ ካለፈው ሐምሌ ወር መጀመሪያ አንሥቶ በተቀሰቀሰ የኮሌራ ወረርሽኝ፣ 90 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ፣ የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

አምስት ሺሕ የሚደርሱቱ ደግሞ፣ በወረረሽኙ ተይዘው ሕክምና እንዳገኙ፣ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮም፣ ወረርሽኙ እንደተከሠተ አረጋግጦ፣ በተለይ በጸበል ቦታዎች እና ሰዎች በብዛት በሚሰባሰቡባቸው አካባቢዎች፣ የከፋ ጉዳት ማድረሱን ጠቅሷል፡፡ ይኹንና በአሁኑ ወቅት፣ በወረርሽኙ የሚሞቱ እንደሌሉ፣ የጤና ቢሮውም ኢንስቲትዩቱም አስታውቀዋል፡፡

አንድ የደብረ ታቦር ስፔሻሊቲ ሆስፒታል የሕክምና ባለሞያ ደግሞ፣ የአካባቢው የጸጥታ ችግር፣ ሕክምና ለመስጠትም ኾነ ሕክምና ለማግኘት አዳጋች እንደኾነ ተናግረዋል፡፡ በተለይ የገጠሩ ኅብረተሰብ ለጉዳት እየተዳረገ እንደኾነ ጠቁመው፣ ተፋላሚ ኃይሎች፣ ለጤና አገልግሎቶች እና ሰብአዊ ድጋፎች መዳረስ ተባባሪ እንዲኾኑ ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG