በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት እና የፋኖ ታጣቂ ለድርድር እንዲቀመጡ አብን “ጥረት እያደረግኹ ነው” አለ

መንግሥት እና የፋኖ ታጣቂ ለድርድር እንዲቀመጡ አብን “ጥረት እያደረግኹ ነው” አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:39 0:00

መንግሥት እና የፋኖ ታጣቂ ለድርድር እንዲቀመጡ አብን “ጥረት እያደረግኹ ነው” አለ

የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/፣በዐማራ ክልል ለተስፋፋው የጸጥታ ችግር መፍትሔው ሰላማዊ ድርድር ነው፤ ሲል አስታወቀ፡፡

ፓርቲው፣ ትላንት ሰኞ ባወጣው መግለጫው፥ በግጭቱ የደረሰው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት እንደሚያሳስበው ገልጿል፡፡ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና ታጣቂዎቹ ወደ ድርድር እንዲመጡ፣ ለጉዳቱም ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በአስቸኳይ ተኩስ እንዲቆምና የተዘጉ መንገዶች ተከፍተው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዲጀምሩም ጠይቋል፡፡

ለድርድሩም ፓርቲው የድርሻውን እየተወጣ እንደኾነ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ ያደረጉት፣ የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው ጣሂር መሐመድ ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG