አዲስ አበባ —
መሰንበቻውን በባህር ዳር እና በአዲስ አበባ ከፍተኛ የመንግስት ባለ ሥልጣናት የተገደሉንባቸውን ድንገቶች ተከትሎ ሁለት የአማራ ተወላጆች ማኅበራት ከዋሽንገተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው የሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ ተንተርሶ የተካሄደ ቃለ ምልልስ ነው።
ማኅበራቱ የአማራ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ እና የአማራ ባለሞያዎች አንድነት ይባላሉ። ሁለቱን ማኅበራት በመወከል የአማራ ማሕበር በሰሜን አሜሪካ የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ አቶ ተመስገን መንግሥቱ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ