በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአብን የፓርላማ አባል ዘመነ ኃይሉ ከሦስት ቀናት እስር በኃላ ዛሬ መለቀቃቸውን ተናገሩ


የአብን የፓርላማ አባል ዘመነ ኃይሉ
የአብን የፓርላማ አባል ዘመነ ኃይሉ
የአብን የፓርላማ አባል ዘመነ ኃይሉ ከሦስት ቀናት እስር በኃላ ዛሬ መለቀቃቸውን ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:06 0:00

ባለፈው ሰኞ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ለእስር ተዳርገው እንደነበር የጠቀሱት የተቃዋሚው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ አባል ዘመነ ኃይሉ ዛሬ መስከረም 23 ቀን 2017 ዓም መፈታታቸውን ተናግረዋል። አቶ ዘመነ በከተማው ከሚገኙት ፖሊስ ጣቢያዎች በአንዱ ከ40 ሰዎች ጋር ታስረው መቆየታቸውን ገልጠው ከእነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ አሁንም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን አመልክተዋል።

በጉዳዩ ከፌደራልና ከክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች ምላሸ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

የታሰሩበትን ትክክለኛ ምክንያት በኋላም እንዴት እንደተፈቱ የሚያውቁት ነገር ለመኖሩን አመልክተዋል።

በተመሳሳይ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት የገዥው ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ መልካሙ ተሾመ ባለፈው ማክሰኞ በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ መለቀቃቸውን አቶ ዘመነ አክለው ገልፀዋል። በሌላ በኩል፣ በአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በጋዜጠኝነት አቶ የሺሃሳብ አበራ፣ ሰኞ መስከረም 20 ቀን 2017 በባህር ዳር ከተማ መታሰሩንና ከሌሎች እስረኞች ጋር ወደ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን የቤተሰብ አባላት ተናግረዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ ከፌደራልና ከክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። በአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢዎች የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምጽ ማጫወቻ ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG