በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራና በኦሮሞ ብሔረሰብ የማረጋጋት ሥራ እየተሰራ ነው


የሀገር መከላከያ ሰራዊት ግጭት ተከስቶ በነበረባቸው በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች በመግባት የመቆጣጠር እና የማረጋጋት ስራ በማከናወን ላይ መሆኑን ገለፀ።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዡር ሹም ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮለኔል ተስፋዬ አያሌው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፣ የክልሉ መንግሥት ባቀረበው ጥሪ መሰረት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢዎቹ ገብቶ የማረጋጋት ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል።

አሁን ላይም አካባቢዎቹ እየተረጋጉ ቢሆንም በመንገድ ዳርቻዎች ላይ አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ እንዳለ ተገልጿል። ከተሞች ወደ መረጋጋት እየገቡ ቢሆንም በገጠራማ አካባቢዎች የተኩስ ልውውጡ እንደሚሰማ ኮሎኔል ተስፋየ ጠቁመዋል።

የግጭቱ መንስኤን ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የማጣራት ሥራ እንደሚከናወን እና ያንን መሰረት በማድረግ አርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አመላክተዋል።

የአትዘጉት የደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ሲናና እና ደብረ በርሃን መንገዶችንም የማስከፈት ሥራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG