በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለደን ምንጣሮ ወደ ሕዳሴ ግድብ የሚያመሩ 275 ወጣቶች መታገታቸው ተገለጸ


ካርታ
ካርታ

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላ እና አሌ ዞኖች የተመለመሉ ወጣቶች ለደን ምንጣሮ ሥራ ወደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በመጓዝ ላይ ሳሉ፣ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ እንደታገቱ ቤተሰቦቻቸው አስታውቀው ደኅንነታቸው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ወጣቶቹ ባለፈው ሳምንት ሰኞ ለጉዞ መነሣታቸውን ያወሱት ቤተሰቦቻቸው፣ መታገታቸውን በማኅበራዊ የትስስር ገጾች ሲዘዋወር ባዩት አጭር ተንቀሳቃሽ ምስል እንደተረዱ ጠቁመዋል።

የጋርዱላ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ኩናኖ ለደን ምንጣሮ ተብለው ከጋርዱላ ዞን ደራሼ እና አሌ ወረዳዎች የተወሰዱ 275 ወጣቶች መታገታቸውን ገልፀዋል።

ለደን ምንጣሮ ወደ ሕዳሴ ግድብ የሚያመሩ 275 ወጣቶች መታገታቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:02 0:00

የወጣቶቹን መታገት ያመኑት የጎጃም ፋኖ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ መሆናቸውን የገለፁት መቶ አለቃ አበበ፣ “ወጣቶቹ ለደን ምንጣሮ የሚንቀሳቀሱ ሳይሆኑ የመከላከያ ሰራዊት እና የሚሊሺያ አባላት ናቸው” ብለዋል።

ወጣቶቹ እንደታገቱበት የተገለጸውን የምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ባለሥልጣናትን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ፣ ስልካቸውን ስለማያነሡ ለማካተት አልተቻለም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG