በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ከብቶች እየሞቱ ነው


በአፍሪካ ቀንድ 11 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል
በአፍሪካ ቀንድ 11 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል

በሶማሊያ የተከሰተው ድርቅ ወደርሃብ መሸጋገሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ

እርዳታ በማይደርስባቸው የሶማሊያ ደቡባዊ ቀጣናዎች ድርቅ ያስከተለው ከፍተኛ የምግብ ዕጥረት ዕለቂት ሊያስከትል ወደሚችል ርሃብ መሽጋገሩን የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ይፋ አደረጉ። የአፍሪካ ህብረትና የዓለሙ ድርጅት የደረሰውን ሰባዊ ቀውስ ለመታደግ በትብብር እንዲንቀሳቀሱ ጠየቁ።

የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጆሴት ሽራም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ኢራስተስ ሞኤንቻ ጋር በመሆን በአፍሪካ ህብረት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በአሁኑ ጊዜ የተከሰተው ድርቅና ያስከተለው ቀውስ መከታተል ድርጅታቸው በዓለም ላይ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ቅድሚያ የሚሰጠው ነው። ድርቁ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶማሊያ ኬንያና ኡጋንዳ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። የዚህ ሰባዊ ቀውስ ዋና ተጠቂ የደቡብ ሱማሊያ ክፍል ነው ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ።

“ ሁኔታው ከባድ ጥፋት እያስከተለ ነው። ሆኖም በቁጥጥር ስር ነው።የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ እየጨመረ ነው። ስለሆነም በማንደርስባቸው አካባቢዎች ካልሆነ በስተቀር የሰው ህይወት አልጠፋም” ብለዋል ሽራም።

“እንዳለን መረጃ ከሆነ ሰባ በመቶ የሚሆነው የሶማሊያ ህዝብ ዕርዳታ ማግኘት በሚችልበት ሁኔታ ላይ አይደለም። ይህ ደግሞ ሰባዊ ቀውስ ፈጥሯል።”

በታሪክ እንደታየው ድርቁ እየከፋ በሄደ ቁጥር ሰባዊ ቀውሱ እየከፋይሄዳል ይላሉ ሽራም። በአፍሪካ ቀንድ ድርቁ በስፋት የደረሰ ቢሆንም የሰው ህወት አልጠፋም ያሉት ጅሴት ሽራም መድረስ ያልተቻለባቸው የሱማሌ አካባቢዎች ግን ድርቁ ወደርሃብ ተሸጋግሯል።

“የአሰራር ፕሮቶኮል የምንመሰርትበትን ብልሃት በማፈላለግ ያስቸኳይ ጊዜ እርዳታዎች አከማችተን በደቡብ ሱማሊያ የችጋር ቀጣናዎች ተብለው ወደተለያዩ አካባቢዎች ለመድረስና ሕይወት ለማዳን እየሞከርን ነው።”

ሚስ ሽራም ይህን ቀውስ ለመፍታት የሚያስፍልገውን እርዳታ ለመሰብሰብ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይገባል ብልዋል።

“የእርዳርታውን ቁሳቁስ ባስቸኳይ ማሰባሰብ ያስፈልጋል። አሁን ያለን ጉድለት $190 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይሄ ደግሞ ለተጠበቀው 6 ሚሊዮን እርዳታ ጠባቂ ህዝብ ነበረ። በግንቦትና ሰኔ ይጠበቅ የነበረው ዝናብ ስላልጣለ ይህ የርዳታ ጠባቂ ቁጥር ወደ 11 ሚሊዮን እንደሚደርስ ይጠበቃል። ይሄ በደቡብ ሶማሊያ ያሉትን ለመድረስ ተስፋ በማድረግ ነው።”

ድርቁ በኢትዮጵያ ያስከተለውን ችግርም በጥልቀት ዘርዝረዋል።

“በኢትዮጵያ በደቡብና ደቡብ ምስራቅ በሚገኙ ሰፊ አካባቢዎች ድርቁ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። በተለይም አርብቶ አደሩ በቀውስ ውስጥ ይገኛል። ይኽ ቀውስ ለረጅም ጊዜ የቆየ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታትም ብዙዎች ከብቶቻቸውን አጥተዋል። ሌሎች በርካቶችም ያላቸውን ሁሉ ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ አጥተዋል። እናም በአርብቶ አደሮች ላይ የደረሰው ቀውስ በጥልቁ ያሳስበናል።”

ዳይሬክተሯ ድርቁ ያስከተለውን ቀውስ ለመቋቋም ከአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጋር በጥልቀት ተወያይተዋል።የህብረቱ ረዳት ኮሚሽነር ኢራስተስ ሞኤንቻም ስለውይይታቸው ትኩረት ይህን ብለዋል።

“ትኩረታችን አሁን በምናየው ቀውስ ላይ ብቻ አይደለም። እንዲህ አይነት ሁኔታን እንዴት መከላከልና ማለዘብ እንችላለን በሚለው የወደፊቱን ጊዜ ጭምር ነው። አቅምን በመገንባት ላይ ዘላቂነት ያላቸው መፍትሄዎች በመዘርጋት ላይ ነበር አተኩረን የተነጋገርነው።”

13 የድርጅቱ ሰራተኞች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ በስራላይ እንዳሉ መገደላቸውን ጆሴት ሽራም አውስተው የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተባብረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG