በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዋልድባ ገዳም አካባቢ የስኳር ልማት በአካባቢው ማህበረሰብ ቁጣ ቀሰቀሰ


ሰዎች በብዛት ወደ ገዳሙ እንደተጓዙ የዓይን ምስክሮች ገለጹ

ለስኳር ልማት ሊውል ወደታቀደበት የዋልድባ ገዳም አካባቢ፤ ህዝብ ከተለያዩ አካባቢዎች እንዳቀና ምስክሮች ገለጹ።

ከተለያዩ የጎንደር ከተሞች የተውጣጡ በርካታ ነዋሪዎች፣ ዋልድባ ገዳም አካባቢ ይሠራል የተባለውን የስካር ፋፍሪካ በመቃወም፤ ወደ ግድቡ መሥሪያ ስፍራ እንደሄዱ ተሰምቷል።

በዚህም የተነሳ አንዳንድ ውዝግብ እንደተቀሰቀሰ ከአካባቢው ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየታቸውን የሰጡ ግለሰቦች ገልጸዋል።

“በሃያም፣ በሃምሳም፣ በመቶም እየሆነ የተመመው ሕዝብ ማንም ያላሰባሰበውና ያላስተባበረው፣ ነገር ግን በራሱ ፈቃድ ጥሩምባ ነፍቶና ሆ ብሎ እንደሆነ” የአይን ምስርክር ገልጸዋል።

እንደምስክሩ አገላለጽ ጦር ያለው ጦሩን፣ መሣሪያ ያለው መሣሪያውን፣ ዶማና አካፋ ያለውም ያንኑ እየያዘ ነው ግድቡ ይሠራል ወደተባለበት ስፍራ የተጓዘው። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን፣ ወታደሮች ወደ ሕዝብ ለመተኮስ እንዳይሞክሩ መንግሥት ማስጠንቀቁንም እኒሁ ምንጭ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አንድ ከዚያው ከገዳሙ አካቢ ያሉ ቄስ «ከወልቃኢትም፣ ከጠገዴም፣ ከአድርቃይም፣ ከማይፀብሪም ባለሥልጣናት ተጠርተው ሥራው ሊቆም ተደራድረዋል፤ ለዚህም ቀጠሮ ለሚያዝያ ፳፱ ተይዟል» ሲሉ ለቪኦኤ ገልጸዋል።

በመንግሥት በኩል ላለው ምላሽ ከዚህ ቀደም አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ በመስጠት ወደተባበሩን፣ የማይፀብሪ አስተዳዳሪ ወደሆኑት ወደ አቶ ሲሳይ መረሣ ዘንድ ደውለን ለጊዜው ስብሰባ ላይ ስለነበሩ ማግኘት አልተቻለም።

XS
SM
MD
LG