በህክምና ትምህርት ረገድ የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት የጤናና የሰብዓዊ አገልግሎቶች መስሪያቤት በአፍሪካ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት በሚቀጥሉት 5 ዓመታት 130 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሰጥ ተገለጸ።
ከሰሃራ በታች ባሉ አገሮችና በዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት መካከል በተገባው የእርዳታ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ትካተታለች።
ማክሰኞለት በአዲስ አበባ በተከፈተ ጉባዔ የተናገሩት በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴይትስ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ መርሃ ግብሩ በዩናይትድ ስቴይትስና በኢትዮጵያ በሚገኙ የህክምና ትምህርት ቤቶች መካከል የትብብር መድረክ ይፈጥራል ብለዋል።
መለስካቸው አምሃ ከአዲስ አበባ ያደረሰንን ዘገባ ያዳምጡ