በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊው ኢማና መርጊያ በሮም ድል ተቀዳጀ


የገባበት 12 ደቂቃ 54 ሴኰንድ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦለታል።

የኢጣልያ ዋና ከተማ ሮም ባስተናገደችው ዓመታዊ የ Golden League ሦስተኛ የከተማ ውድድር በወንዶቹ 5 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያዊው ኢማና መርጊያ ድል ተቀዳጅቷል።

የገባበት 12 ደቂቃ 54 ሴኰንድ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦለታል።

በጉዳት ምክንያት ለስምንት ወራት ከውድድር ርቆ የቆየው ጃማይካዊው ፈጣን ሯጭ Usai Bolt በ 9 ነጥብ 9 1ያገሩን ተወላጅ Assafa Powellን ቀድሞ ገባ።

በእግር ኳስ ስፖርት፥ በማራኪ የአጭርና የረዥም ቅብብል ጨዋታው የሚደነቀው የስፔኑ ባርሴሎና ከሜዳው ውጭ የእንግሊዙን ማንቼስተር ዩናይትድ 3 ለ 1 አሸንፎ ትልቁን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አነሳ። ደጋፊዎቹን አስፈነደቀ።

ዓለምአቀፉ የእግር ኳስ ማህበር FIFA ከነገ በስቲያ ረቡዕ ዙሪክ ላይ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ያካሂዳል። በማህበሩ ውስጥ ሙስና ተንሠራፍቷል የሚለው ዜና በምርጫው ላይ አጥልቷል።

ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG