በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በመካከለኛው ምሥራቅና ሰሜን አፍሪቃ ሀገሮች ለውጦች ላይ ንግግር አድርጉ።


የሁዋይት ሐውስ ቤተ መንግሥት በአካባቢው ሀገሮች እየተካሄዱ ያሉ አብዮቶች፥ ለዘመናት የፖለቲካና ኢኰኖሚ ነፃነት ተነፍገው ለቆዩ ሕዝቦች ፍላጐት መሳካት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ብሏል።

ብዙ ሙስሊማን በዩናይትድ ስቴትስ ላይ እንዲያመሩ ካደረጓቸው ምክንያቶች በቁልፍነት የሚጠቀሱት ሦስቱ፥

- የቡሽ አስተዳደር በኢራቅ ላይ ጦርነት ማወጅ፥
- የጓንታናሞ ቤይ ኪዩባና አቡ-ግሬይብ እሥር ቤቶች አያያዝና ፖሊሲው፥ እንዲሁም
- በፍልሥጤማውያንና እሥራኤል ግጭት ወደ እሥራኤል ያዘነበለ የሚሉት ፖሊሲ ናቸው።

ፕሬዘዳንት ኦባማ የዛሬ ሁለት ዓመታት ግድም ግብፅን በጐበኙበት ወቅት በዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያተኰረ ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል። በነዚህ መሠረታዊ መርሆዎች መጠበቅ ላይ ከጐናችሁ ነን ሲሉ ነበር ላካባቢው ሀገሮች ሕዝቦች ቃል የገቡት።

ያ የፕሬዘዳንቱ ቃል አልተጠበቀም ነው የሚሉት ዛሬ የመካከለኛው ምሥራቅና የሰሜን አፍሪቃ ሀገሮች ሕዝቦች። አሁን ከቱኒዝያ እስከ ባሕሬን የተቀጣጠለውን በተለይ የየመኑን ሕዝባዊ አመጽ አስመልክቶ የኦባማ አስተዳደር የሰጠው ምላሽ በጣም የዘገየና አንዳንዱም ፈጽሞ ቸል የተባለ ነው ሲሉ ያማርራሉ።

ፕሬዘዳንቱ በዛሬው ንግግራቸው ግን በተለይ ለአምባገነን መንግሥታት ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ የትኛውንም የዜጐቹን ለዲሞክራሲና ለውጥ ያለውን ፍላጐት በኃይል ለማገድ የሚሞክር፥ የሰብዓዊ መብቶችን የሚጥስ መንግሥት ትቃወማለች ብለዋል።

የዛሬውን የፕሬዘዳንቱን ንግግር የፖለቲካ አጥኚ በሆኑት በአቶ ጁዋር መሐመድ በአስገምግመናል።

ውይይቱን ከዚህ ያድምጡ።





XS
SM
MD
LG