በአፍሪቃ ከፍተኛውን የሕዝብ ቁጥር በያዘችው በናይጄሪያ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ እንደሚያሸንፉ የሚጠበቀው የወቅቱ መሪ Goodluck Jonathan ሥልጣን የያዙት ባለፈው ዓመት የቀድሞው ፕሬዘዳንት Umaru Yar’Adua በሞት ከተለዩ በኋላ መሆኑ ይታወሳል። ሚስተር Jonathan ያኔ ምክትል ፕሬዘዳንት እንደነበሩም አይዘነጋም።
ነፃው የናይጄሪያ ብሄራዊ የምርጫ ኰሚሽን ምንም እንኳ ከአንድ ወር በፊት አጠቃላይ ምርጫው ሲጀመር ብዙ እንቅፋቶች አጋጥመው እንደነበር ቢታወቅም፥ የነገውን ምርጫ ለማካሄድ ግን ተዘጋጅቼአለሁ ብሏል።
ባለፈው ሳምንት ሀገሪቱ ውስጥ የተካሄዱት የፓርላማ ምርጫዎች በሎጂስቲክስና በድምፅ መስጪያ ሳጥኖች ሥርጭት ችግር ለሁለት ጊዜ ተራዝመዋል። ባሁኑ ጊዜ ግን ሰባ ሚሊዮን መራጮች በነገው ዕለት ድምፅ መስጠት እንደሚችሉ ኰሚሽኑ አስታውቋል።
ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ