በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግሥቱ ሚዲያ፥ የሕዳሴ ግድብ እና የኑሮ ውድነት በኢትዮጵያ


የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለግድቡ ግንባታ በተጋነነ መልክ ሰፊ ሽፋን እየሰጡ ያሉት በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ላይ የሚታየውን አስከፊ የኑሮ ውድነት አጀንዳ ለማስቀየር ታሰቦ ነው ይላሉ ተቃዋሚዎች። መንግሥት ግን ካለማወቅ የሚሰጥ ግምት ነው ሲል ውድቅ ያደርገዋል።

የሕዳሴ ግድብ ግንባታው እቅድ ድንገት ዱብ ያለው በሰሜን አፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የተከሰተውን ዓይነት ሕዝባዊ አመፅ ኢትዮጵያም ውስጥ እንዳይከሰት ለመከላከል የተፈጠረ አጀንዳ ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች ለሚያቀርቡት ትችት ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ለሚዲያ ምላሽ ሰጥተዋል።
የግድቡ ግንባታ ጉዳይ ቀደም ብሎ የታቀደ እንጂ በድንገት የመጣ አለመሆኑን፣ ሕዝባዊ አመጽ ይከሰታል ብሎ የፈራ መንግሥትም በኑሮ ውድነት የተቸገረን ሕዝብ ገንዘብ አዋጣ እንደማይል ይገልጻሉ።

የዛሬው የዲሞክራሲ በተግባር እንግዳ አቶ ገብሩ አሥራት የወቅቱ የመድረክ ሊቀ መንበር ከአዲስ አበባ ናቸው። እርሣቸው በበኩላቸው ደግሞ ሚዲያው በተለይ የመንግሥቱ ራዲዮና ቴሌቪዥን ቀንና ማታ ያለማቋረጥ ሰፊ ሽፋን እየሰጡ ያሉት ሕዳሴ ለሚሉት ግድብ ግንባታ እንጂ ባሁኑ ወቅት ህብረተሰቡን እየተፈታተነ ላለው ከባድ የኑሮ ውድነት አይደለም። መንግሥት ከመጀመሪያው ጀምሮ ለኑሮ ውድነት ችግር መፍትሔ የሚሰጡ አቅጣጫዎችን አለመከተሉ ነው የኑሮ ውድነቱን ያባባሰው ብለዋል።

ሙሉ ቅንብሩን ከዚህ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG