እንደ አዉሮፓ አቀጣጠር በሃምሌ ወር ሁለት ሺህ ስድስት በርካታ ከፍተኛ መኮንኖችና ወታደሮችን ይዘዉ ከኢትዮጵያ ሰራዊት በከዱት ጄነራል ከማል ገልቹ የሚመራዉ የአሮሞ ነጻነት ግንባር፣ ወቅታዊ የሆነዉን አብሮ የመስራት ወቅታዊ የማኅበረሰብ ጥያቄ በመቀበል ለኢትዮጵያ ዜጎች ሁሉ መብት መከበር በአንድነት ጥላ ስር እታገላለሁ ሲል ከትላንት በስቲያ ታህሳሳ 22 መግለጫ አዉጥቷል።
ለረጅም ዓመታት በአቶ ዳኡድ ኢብሣ የተመራዉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በበኩሉ፤ ቡድኑን ”አናሳ ተገንጣይ” በማለት የድርጅቱን ስም ለመጠቀም ህጋዊና ሞራላዊ መሰረት የለዉም፣ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ የተለየ ስለሆነ የምንታገለዉ ነጻነት ጭምር የእራሳን እድል በራስ ለመወሰን ሲል ዛሬ የተቃዉሞ መግለጫ አዉጥቷል። በአቶ ዳኡድ ኢብሳ ወገን ከሚመራዉ የድርጅቱን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልና ቃል አቀባይ ዶክተር በያን አሶባን፣ በጄነራል ከማል ገልቹ ከሚመራዉ ቡድን ደግሞ የዉጪ ጉዳይ ሃላፈ የሆኑትን አቶ ቃሲም አባ ነሻን ትዝታ በላቸዉ አነጋራለች።