የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የህንድ ባለጸጎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በልማት ስራ እንዲሳተፉ አበረታቱ። የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞንሞሐን ሲንግ አቶ መለስ ህንድን እንዲጎበኙ ጋብዘዋቸዋል።
ሁለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች በሀገሮቻቸው ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገው ሲያበቁ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አንዳንድ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በትላልቅ የርሻ ልማቶች ላይ መሳተፍን በተመለከተ ጥርጣሬ እየገባቸው ነው፥ ይህ ህንዳውያንንም ይመለከታል ተብሎ ከጋዜጠኛ ለቀረበ ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት መቀራመት ኖሮ አያውቅም ወደፊትም አይኖርም ማለታቸው ተጠቅሷል።
ዝርዝር ዘገባውን ያድምጡ