ኬንያ በሚቀጥለው ሣምንት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች። በዚህ ምርጫ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋና የአሁኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ይፎካከራሉ።
ሁለቱም ዕጩዎች የኬንያን ምጣኔኃብት ለማሻሻልና ሙስናን ለመዋጋት መላ እንዳላቸው እየተናገሩ ነው።
ይሁን እንጂ የመገለባበጣቸው ነገርና ከቀደም ምርጫዎች ጋር በተያያዙ ሁከቶች ውስጥ እጆቻቸው እንዳሉ የሚቀርቡባቸው ክሦች በአመራር ብቃታቸው ላይ ጥያቄ እያስነሱ ነው።
ቪክቶሪያ አሙንጋ ከናይሮቢ ያጠናቀረችውን ዘገባ ደረጀ ደስታ ወደ አማርኛ መልሶታል።