በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኑሮ ውድነት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሰጡት ማብራሪና የባለሙያዎች ትንተና


ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በፓርላማ ቀርበው በሰጡት የአገሪቱ ሁኔታ መግለጫ፤ በምጣኔ ሃብት ዙሪያ ያተኮረው ንግግራቸው በዋጋ ንረት ላይ ነበር።

የገንዘብ ዋጋ ማጣት ወይንም ግሽበት መንስዔዎችን ከዚህ ቀደም በነበሩ የፓርላማ ንግግሮቻቸው ዘርዝረው፤ ለኢትዮጵያ የግሽበት መንስዔ ግን የሚበዛው በገበያ ስርዓቱና ከውጭ በሚመጣ የዋጋ ጭማሪ መሆኑን ሲያሰምሩበት የቆዩት አቶ መለስ፤ በዘንድሮው ንግግራቸው በባለሙያዎች አስተያያት “በግልጽ ችግሮቹን ያመኑበት” ንግግር ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ላይ በመመርኮዝ በመሪ ስቴይት ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ፕሮፌሰር ሰይድ ሃሰንንና የካርኒጊ ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ሽመልስ መኮንን ጋር ያደረግንውን ውይይት ያዳምጡ

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG