በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግስት የፍትህና ፍኖተ ነጻነት ጋዜጦችን ማፈኑን ያቁም ሲል ኢትዮጵያዊ የመብት ድርጅት ጠየቀ


የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ የኢትዮጵያ መንግስት የመናገር ነጻነትን እያፈነ ነው ብሏል

የኢትዮጵያ መንግስት በቀጥታና በተዘዋዋሪ መልኩ በግል ጋዜጦች ላይ የሚያሳድረው ጫና በአገሪቱ የቀሩ በጣት የሚቆጠሩ ጋዜጦችንና የመናገር ነጻነትን ያፈነ ነው ሲል የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አስታወቀ።

በፍትህና ፍኖተ ነጻነት ጋዜጦች ላይ ተደረገ ያለውን፤ የመብት ጥሰት ድርጅቱ የቅድመ-ምርመራ አሰራርን የተከተለ ብሎታል።

“ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ሽፋን እና ተነባቢነትን እያገኘች የመጣችውን የፍትህ ጋዜጠ የሀምሌ 13 እትሙ በፍትህ ሚኒስትር እንዳይወጣ ከመደረጉም ሌላ ማቀጣዩ የጋዜጣዋ ህትመቶችም እንዳይወጡ የመንግስት ንብረት የሆነው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጥሯል” ይላል የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ያወጣው መግለጫ እስክንድር ፍሬው ዝርዝሩን ከአዲስ አበባ ያስተላለፈውን ዘገባ ያዳምጡ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG