በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለአፍሪካ ቀንድ ድርቅ ተጠቂዎችና ስደተኞች ዩናይትድ ስቴይትስ ድጋፏን እንድትቀጥል ተጠየቀ


በዩናይትድ ስቴይትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚገኝ ሸንጎ፤ በአፍሪካ ቀንድ በድርቅ ለተጎዱ ሰዎች ምግብና ሌሎች አቅርቦቶች የማድረስ ጥረቱ እንዲቀጥል አሳሰበ።

በአፍሪካ ቀንድ የቀጠለውን የስደተኞች ሁኔታ ለመመርመር የዩናይትድ ስቴይትስ የህግ መምሪያው ቡድኖች በትናንትናውለት ያደመጡትን የምስክሮችን ቃል ያስተባበሩት፤ የቶም ላንቶስ የሰብዓዊ መብት ኮሚሺን እና በቤቱ የረሃብ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ናቸው።

የኮሚቴው አጋር ሊቀ-መንበር የማሳቹሴትሱ ዴሞክራት ጄምስ ምክገቨርን በመክፈቻ ንግግራቸው፤ ባለፈው ወር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሶማሊያ ረሃብና ቸነፈሩ አብቅቷል ብሎ ቢያውጅም ድርቁና ተዛማጅ የስደተኞች ችግሮች አሁንም በስፋት ይታያሉ ብለዋል።

“በጦርነትና በረሃብ የተንሳ ወደ 2.5 ሚሊዮን ሶማሊያዊያን በአገር ውስጥና ወደ ጎረቤት አገሮች ተሰደዋል። በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የተቸገሩ ሰዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በአካባቢው የስደተኞች ቀውስ ፈጥሯል።”

የዩናይትድ ስቴይትስ የአለም አቀፍ ተራድዖ USAID ከፍተኛ ባለስልጣን ናንሲ ሊንቦርግ፤ በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን ድርቅ ለመታደግ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ አሰራሮች ሚና ተጫውተዋል ብለዋል። ረሃቡና ቸነፈሩ በሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያና ኬንያ በተባባሰበት ወቅት 935 ሚሊዮን ዶላር አሰባስቦ ለአስቸኳይ የምግብ፣ የመጠለያ፣ የጤናና የመሳሰሉ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማሟያ እንደዋለ ሊንቦርግ ገልጸዋል።

“በእውነቱ ባለፉት 60 ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ አስቸኳይ የሰብዓዊ እልቂት ከፊታችን ተደቅኖ፤ በምን ያህል ፍጥነትና ብቃት ተደራጅተን ምላሽ እንደሰጠን ሳስበው ይደንቀኛል። ለውጥ አምጥተናል።”

ሊንቦርግና ሙያዊ አስተያየታቸውን የሰጡ የኦባማ አስተዳድር ባለስልጣናት፤ የአፍሪካ ቀንድ አሁንም የአለማችን ትልቁ የስደተኞች ቁጥር ያለበት አካባቢ መሆኑ አሳስበዋል። ድርቁ ጋብ ቢልም ቀጣይ የመልሶ ማቋቋም ስራዎችና ድርቅና ረሃብን እንዲሁም ጦርነት ሽሽት የተሰደዱ ሰዎች እለታዊ ፍላጎቶችን ማሟላትም ትኩረት እንደሚያሻው አስምረውበታል።

ማርጋሬት መክሊቪ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ እርዳታ ቢሮ ሃላፊ ናቸው። ሶማሊያዊያን ስደተኞችን ጎረቤት አገሮች እንዲቀበሏቸው ማድረግ ከባድ ፈተና መሆኑን ይገልጻሉ።

“የሶማሊያዊያን ስደተኞችን አስመልክቶ ያለብን ትልቁ ፈተና በጎረቤት አገር ጥገኝነት ማግኘት ነው። ለምሳሌ ጅቡቲ ወታደር ለመሆን እድሚያቸው የደረሱ ሶማሊያዊያንን ላለመቀበል ወስናለች።”

መክሊቪ አክለውም ሲያስረዱ፤ የኬንያ መንግስት ነጻ በወጡ የሶማሊያ ግዛቶች የሰብዓዊ እርዳታ ቀጠና ተዘጋጅቶ ስደተኞች በዚያ እንዲሰፍሩ እየጠየቀ ነው ብለዋል። ሆኖም በርካታ ሶማሊያዊያን ደህንነታቸው እንዲጠበቅና በሰላም እንዲኖሩ አገራቸውን ምልቀቅ እንዳለባቸው ባለስልጣኗ አስታውቀዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ ዴብራ ማላክ፤ ድርቁ በአፍሪካ ቀንድ የምግብ እህል እጥረት እንዳስከተለ አብራርተዋል። ሆኖም በድርቁ ሳቢያ በርካታዎች እንዲሞቱና እንዲሰደዱ ምክንያት የሆነው የሶማሊያ የእስልምና አንጃ አልሸባብ መሆኑን ይገልጻሉ።

“አልሸባብ በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች እርዳታ እንዳይደርስና የድህንነቱን ሁኔታ አስጊ በማድረጉ፤ የነበረው ድርቅ ወደለየለት ገዳይ ረሃብና ቸነፈር ተሸጋግሯል። በዚያ ላይ ለአመታት የዘለቀው ጦርነት ሶማሊያዊያን ድርቅን ለመቋቋም ለዘመናት ያዳበሯቸውን መንገዶች ሁሉ አክስሞባቸዋል።”

በሶማሊያ ድርቁ ክፉኛ በርካታ ሰዎችን ከጎዳባቸው አካባቢዎች 60 ከመቶ የሚሆኑት በአልሸባብ ቁጥጥር ስራ ያሉ አካባቢዎች ናቸው። የእስላማዊ አንጃው በጦርነት በታመሰችው የአፍሪካ ቀንዷ አገር ጥብቅ የእስላማዊ አስተዳድር ለመመስረት ይታገላል። የዩናይትድ ስቴይስት መንግስት አልሸባብን ከአሸባሪው አልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳ

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG