በጂማ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው የአሰንዳቦ ከተማ በርካታ ቤተክርስቲያኖች በሙስሊሞች መቃጠላቸውን አማኞች ይናገራሉ። ሰፊ ማጣራት በሚካሄድበት ወቅት የኢትዮጵያ የእስልምና ሀይማኖት መሪዎች ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው ገልጸው፤ አጠቃላይ መልእክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ የእስምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት ሐጂ ጀማል መሀመድ ሳልህ እስልምና ሰላማዊ ሀይማኖት ነው ካሉ በኋላ፤ ምንም እንኳን በአሰንዳቦ በዝርዝር የተፈጠረውን ለማወቅ ባይቻልም፤ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት በማቃጠልና በመግደል እንደማያምኑ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሀይማኖት መሪዎች የጋር መድረክ አማካሪ የሆኑትን ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ሀርሄ 11 ቤተክርስቲያኖች በጠቅላላው መቃጠላቸውን ከምንጮቻቸው ማረጋገጣቸውን ነው የሚናገሩት።
መንግስት የራሱን ማጣራት ካደረገ በኋላ፣ የሃይማኖት መሪዎች ተሰባስበው እንዲህ መሰል ችግሮችን በጋር ለመፍታት ሊነጋገሩ ይገባል ይላሉ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ።