በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢና ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተሞች ውስጥ በመንግሥት ኃይሎችና የመንግሥት ባለሥልጣናት "ሸኔ" በሚሏቸው፣ እራሳቸውን “የኦሮሞ ነፃነት ጦር” እያሉ በሚጠሩት ታጣቂዎች መካከል ዛሬ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን ቪኦኤ ያነጋገራቸው የከተሞቹ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጋምቤላ ከተማ ውስጥም ከማለዳ ጀምሮ እስከ ረፋድ የቆየ የተኩስ ድምፅ መሰማቱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
የጋምቤላ ክልል ኮምዩኒኬሽንስ ፅህፈት ቤት ዛሬ በማኅበራዊ መገናኛ ገፁ ላይ ባሠፈረው ፅሁፍ "በጋምቤላ ከተማ ተኩስ ከፍተው በነበሩ የሸኔና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ላይ እርምጃ ተወስዷል" ሲል ብሏል።
የኦሮምያ ክልል ባለሥልጣናት ደግሞ ጊምቢና ደምቢ ዶሎ ውስጥ ተፈጥረዋል ስለተባሉት ሁኔታዎች መረጃ እንደሌላቸው አመልክተዋል።
በሌላ በኩል ግን “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” እንደሆነ የሚናገረው ቡድን ዓለምአቀፍ ቃል አቀባይ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ኦዳ ተርቢ ዛሬ በማኅበራዊ መገናኛ ገፃቸው ላይ ባወጡት ፅሁፍ ከጋምቤላ ነፃነት ግንባር ጋር በመሆን ደምቢ ዶሎ ከተማ ላይ የጋራ ዘመቻ እያካሄዱ መሆናቸውን ገልፀል። ናኮር መልካ ዝርዝሩን ይዟል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ዲሴምበር 08, 2023
የሩስያ የአፍሪካ ቀንድ ተጽእኖ እየጨመረ እንደኾነ ምሁራን ገለጹ
-
ዲሴምበር 08, 2023
ባይደን የዩናይትድ ስቴትስ ነባር ማኅበረሰቦችን በገንዘብ እንደሚደግፉ አስታወቁ
-
ዲሴምበር 08, 2023
የፑቲን የአረብ ሀገራት ፈጣን ጉብኝት “የማግለል ጫናን የመቃወም ጥረታቸውን ያሳያል”
-
ዲሴምበር 08, 2023
ኒዤር የፍልሰተኞች ሕጓን በመሻሯ የአውሮፓ ኅብረት ስጋት ገብቶታል
-
ዲሴምበር 08, 2023
በ“ብሔር ብሔረሰቦች ቀን” መከበር ምሁራን የሕገ መንግሥቱን ሚና ይጠይቃሉ