በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢና ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተሞች ውስጥ በመንግሥት ኃይሎችና የመንግሥት ባለሥልጣናት "ሸኔ" በሚሏቸው፣ እራሳቸውን “የኦሮሞ ነፃነት ጦር” እያሉ በሚጠሩት ታጣቂዎች መካከል ዛሬ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን ቪኦኤ ያነጋገራቸው የከተሞቹ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጋምቤላ ከተማ ውስጥም ከማለዳ ጀምሮ እስከ ረፋድ የቆየ የተኩስ ድምፅ መሰማቱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
የጋምቤላ ክልል ኮምዩኒኬሽንስ ፅህፈት ቤት ዛሬ በማኅበራዊ መገናኛ ገፁ ላይ ባሠፈረው ፅሁፍ "በጋምቤላ ከተማ ተኩስ ከፍተው በነበሩ የሸኔና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ላይ እርምጃ ተወስዷል" ሲል ብሏል።
የኦሮምያ ክልል ባለሥልጣናት ደግሞ ጊምቢና ደምቢ ዶሎ ውስጥ ተፈጥረዋል ስለተባሉት ሁኔታዎች መረጃ እንደሌላቸው አመልክተዋል።
በሌላ በኩል ግን “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” እንደሆነ የሚናገረው ቡድን ዓለምአቀፍ ቃል አቀባይ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ኦዳ ተርቢ ዛሬ በማኅበራዊ መገናኛ ገፃቸው ላይ ባወጡት ፅሁፍ ከጋምቤላ ነፃነት ግንባር ጋር በመሆን ደምቢ ዶሎ ከተማ ላይ የጋራ ዘመቻ እያካሄዱ መሆናቸውን ገልፀል። ናኮር መልካ ዝርዝሩን ይዟል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ማርች 10, 2025
የአሜሪካ ታጋቾች ተደራዳሪ ከሐማስ ጋራ የነበራቸውን ንግግር “ጠቃሚ” ብለውታል
-
ማርች 09, 2025
"ከከተሞች ውጭ ያሉ አካል ጉዳተኞችም ትኩረትን ይሻሉ" - ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ
-
ማርች 09, 2025
አትሌቶችን በማፍራት ያለእድሜ ጋብቻን የሚከላከለው ተቋም
-
ማርች 09, 2025
የንጽሕና መጠበቂያ አቅርቦት ለማሻሻል ያለመችው ወጣት
-
ማርች 08, 2025
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማርች 8ትን በሴቶች ብቻ በሚደረጉ በረራዎች እያከበረ ነው