በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሳውዲ እስር ቤት የኢትዮጵያውያን እንግልት በዋሽንግተን አደባባይ አስወጣ


«ያላግባብ የታሰሩ ዜጎቻችን ይለቀቁ፤» ያሉ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና አንዳንድ የመብት ተከራካሪዎች በሳውዲ አረቢያ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማስፈታት በሳውዲ ኤምባሲ ደጃፍ ሰልፍ አካሄዱ።

ያለ ወንጀላቸው ታስረው ለከፋ እንግልት የተዳረጉት ከሰላሳ በላይ ሰዎች ነጻ ይለቀቁ ዘንድ ዩናይትድ ስቴትስ በሳውዲ መንግስት ላይ ጫና እንድታደርግ ከውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትና ከምክር ቤቱ የሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር መነጋገራቸውንም አመለከቱ።

የዘገባውን ዝርዝር ቀጥሎ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG