ሊቢያ ያሉ ኢትዮጲያውያን ስደተኞች በብጥብጥ እየታመሰች ካለችው ከዚያች ሀገር በምን ቀዳዳ እንደምንወጣ ጨንቆናል እያሉ ናቸው።
መዲናዋ ትሪፖሊ ውስጥ ያሉበት አካባቢ ህብረ ብሔራቱ የአየር ጥቃት ዒላማ ከሆኑት ስፍራዎች ቅርብ ቦታ መሆኑን የተናገረው የሃያ ዘጠኝ ዓመቱ ወጣት ሁሴን ኡስማን የመንፈቅ ልጁንና ባለቤቱን ይዞ በከባድ ፍርሃት ላይ እንዳለ ገልጿል።
የሊቢያው ግጭት ከተጀመረበት ጊዜ አንስተው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ለማስወጣት ጥረት ሲያደርጉ የቆዩት የሮማ ካቶሊክ ቤት ክርስቲያን አባት እና የአዣንሲያ አበሻ ግብረ ሰናይ ድርጅት መስራች አባ ሙሴ ዘርዓይ ባሁኑ ጊዜ ያላቸው አማራጭ ወደቱኒዥያ መሄድ ብቻ መሆኑን መክረዋቸዋል ። ወደዚያ ለመድረስ ሲነሱ ጥቃት እንዳይደርስባቸው በትሪፖሊ ባለው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አማካይነት የቀይ ጨረቃ ድርጅት እንዲጠየቅ የሚያደርጉ መሆኑን አባ ሙሴ ዘርዓይ ገልጸዋል።