በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሸባሪነት የተጠረጠሩ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ


በሌሉበት የተከሰሱት ሁኔታው “ኢህአዴግ ጥላው እንደሚያስድነብረው ያሳያል” ሲሉ አጣጣሉት

ሀሙስለት በልደታ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተከሳሾች የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች፣ ጋዜጠኞችና ወታደሮችን ያካተቱ ናቸው።

ከእነዚህ 24 ተከሳሾች መካከል በሀገር ውስጥ የተያዙት ታስረው ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፤ በውጭ አገር የሚኖሩት በሌሉበት ጉዳያቸው ታይቷል።

ሁሉም ተከሳሾች የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም በማሴር፣ በማቀድና በድብቅ በመንቀሳቀስ ተከሰዋል። በተለይ ይላል ይክሱ ይዘት “ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት በተፈረጀው እንዲሁም ኢትዮጵያን ለማተራመስ አቅዶ በሚንቀሳቀሰውና በጦርነት ሁኔታ ላይ ከሚገኘው የኤርትራ መንግስት የሎጅስቲክ፣ ወታደራዊና የፍይናንስ ድጋፍ በሚደረግለት እና ከሌሎች . . .” ኦ.ነ.ግ፣ ኦ.ብ.ነግ. እና ግንቦት 7 አሸባሪ ድርጅቶች ጋር በመስራት፣ አመራር በመስጠትና በሀገር ውስጥ ብህቡዕ መንቀሳቀስ የሚሉ የወንጀል ዝርዝሮችን ያካተተ ነው።

በዚህ የክስ መዝገብ ከተካተቱት መካከል ስድስቱ ጋዜጠኞች ናቸው። በኒውዮርክ መሰረቱን ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ቡድን CPJ የጋዜጠኞቹን ክስ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ላይ ያነጣጠረው “አፋኝ” ጥቃት ብሎታል።

በዚህ የክስ መዝገብ የመንግስቱ ፖሊሲን በመተቸት የሚታወቀው የብሎግ ጸሃፊ እስክንድር ነጋ፣ የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች የነበሩት መስፍን ነጋሽና አቢይ ተክለማርያም፣ በውጭ አገር የሚሰራጩ የሬድዮ ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰሩት አበበ ገላውና አበበ በለው፣ የኢሳት አዘጋጅ ፋሲል የኔአለም ይገኙበታል።

ከሚታወቁ የፖለቲካ መሪዎች የግንቦት 7 መስራችና መሪ ዶር ብርሃኑ ነጋና የአንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አንዷለም አራጌ ይገኙባቸዋል።

በዚህ የክስ መዝገብ በሌሉበት የተከሰሱ ሶስት ግለሰቦች ጋር ያደረግንውን ውይይት ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG