በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግብጽ በኩል ስለ ኢትዮጵያ የነብረው አመለካከት የተሳሰተ እንደሆነና አሁን አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ የመክፈት ፍላጎት እዳላቸው ግብጻውያን ገለጹ።


የግብጽ የህዝባዊ ዲፕሎማሲ ቡድንና የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በቅርቡ ኢትዮጵያን ጎብኝተው ከኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ የኢትዮጵያና የግብጽ ግንኙነት የመሻሻል ምልክት እያሳየ መሆኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል።

"በፊት ግን በግብጽ በኩል በኢትዮጵያ ላይ ከፍታኛ ጥርጣር ነው ሰፍኖ የቖየው። ለ 1700 አመታት አከባቢ የቆየ ጥርጣሬ ነው የነበረው። ስለሆነም በተከታታይ የሚመጡ የግብጽ መንግስታት ኢትዮጵያ የአባይ ውሃን የመጠቀም መብት እንደሌላት ከቅኝ ገዢዎች ጋር የተዋዋሉት ውል ለዘላላም እንደሚቆይ አሁንም ተግባራዊ መሆን ያለበት አድረገው ያዩት ነበር" ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስገንዝበዋል።

XS
SM
MD
LG