በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በአንድ የመንግስቱ ሃያሲ እድሜ ልክ በጋዜጠኞች ላይ ከባድ እስራት በየነ


ህገመንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይልና በሽብር ድርጊት ለመጣል አሲረዋል በሚል በቀረበባቸው ክስ አስቀድሞ ጥፋተኛ የተባሉት ተከሳሾች ሀሙስለት የቅጣት ብይን ተላልፎባቸዋል።

በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴይትስ የሚታተመው የኢትዮጵያን ሪቪው ብሎግ መስራች ኤልያስ ክፍሌ እድሜ ልክ እስራት ተበይኖበታል። በሌለበት የተከሰሰው ኤልያስ ምርጫ 97ትን ተከትሎ ተመሳሳይ ይዘት ባለው ክስ የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖበት ነበር።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዮት አለሙ እና የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅ ውብሸት ታየ ይገኙባቸዋል። እያንዳንዳቸው የ14 ዓመት እስራትና የ33ሽህ ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ዘሪሁን /እግዛአብሄር 17 አመት እና 50 ሺብር፣ እንዲህም ሂሩት ክፍሌ 19 አመት ተፈርዶባቸዋል፡፡

የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG