በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአንተኒ ብሊንከን የአዲስ አበባ ጉብኝት


የአንተኒ ብሊንከን የአዲስ አበባ ጉብኝት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:47 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን የአዲስ አበባ ጉብኝት፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሳቢያ ሻክሮ የቆየው የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት እየተሸሻለ መሄዱን እንደሚያሳይ አንድ የምጣኔ ሃብት ባለሞያ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

ባለሞያው አክለውም የሃገሮቹ ግንኙነት መሻሻል፣ በተለይ በጦርነቱ ለደቀቀው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዲሁም ለመልሶ ግንባታ ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አብራርተዋል። መሰረቱን በአሜሪካ ያደረገው የኢንቨስትመንት ተቋም ፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ዓለም አቀፍ ሊቀመንበርና የምጣኔ ኃብት ባለሞያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያለው ግንኙነት መሻሻል ካሳየ የሚመጡ ምጣኔ ሐብታዊ ለውጦች ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል።

የብሊንከንን ጉብኝት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ሞሊ ፊ፤ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ የማደስ ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህ ግን “ሀገሪቱን ለብዙ አስርት ዓመታት ወደ ኋላ የጎተተውን በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተመሰረተ የግጭት አዙሪት ለመስበር የሚያስችሉ እርምጃዎችን ከኢትዮጵያ እንፈልጋለን፤” ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG