በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ሁለት ገጽታ ያለው ፖሊሲ ታቁም ሲሉ ሰልፈኞች ጠየቁ


የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት በሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያለው አቋም በቻይናዊው ማየት የተሳነው የሰብዓዊ መብት ጠበቃ፤ ከጥያቄ ውስጥ በገባበት ወቅት ኢትዮጵያዊያንም ተመሳሳይ ጥያቄ አንስተዋል።

ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካ የሰብዓዊ መብት ይዞታው ከለት ወደለት እያተበላሸ ነው ለሚሉት የኢትዮጵያ መንግስት የምትሰጠውን ድጋፍ፤ ከመርሆዎቿ ጋር ታጣጥም ሲሉ ጠይቀዋል።

ሰልፉን ያስተባበሩት የኢሕአፓ ወጣቶች ክንፍና ሌሎች የማህበረሰብ ድርጅቶች መሆናቸውን የገለጸው የሰልፉ አስተባባሪ ታዘበው አሰፋ በኢትዮጵያ ገዳማት መቃጠላቸውና ለግብርና ልማት መዋላቸው፣ በአርሲ ሙስሊሞች ላይ ፖሊስ የፈጸመው ግድያ፣ ከደቡብ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎችና በጋምቤላ አካባቢ የሚታየው የመብት ጥሰትና ግድያ አሳስበዋቸው እንደሆነ ገልጿል።

ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG