የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ «ለአፍሪቃውያን ግብረ-ሰዶማዊ ወንዶች የቆመ ድርጅት» የተባለው ቡድን፣ በአዲስ አበባ የሚያደርገውን ስብሰባ በመቃወም ሊሰጡ ያቀዱትን መግለጫ ለሌላ ጊዜ አስተላለፉት።
የፊታችን እሑድ በሚጀመረው ዓለማቀፍ የኤድስ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ በአዲስ አበባ እንደተገኙ የተለጸው የድርጅቱ ተወካዮች፣ ይህን ስብሰባቸውን የሚያሂዱት፣ ከHIV ጋር በማያያዝ እንደነበርም ታውቋል።