በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶር እሌኒ ገብረ-መድህን ከምርት ገበያ ስራአስኪያጅነታቸው በሃምሌ ወር ይለቃሉ


የኢትዮጵያ የምርት ገበያ ነጋዴዎች
የኢትዮጵያ የምርት ገበያ ነጋዴዎች

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ መስራችና ስራ አስኪያጅ ዶር እሌኒ ገብረመድህን ከምርት ገበያ ስራ አስኪያጅነታቸው በሂደት ሊለቁ እንደሆነ የምርት ገበያው አስታወቀ።

የምርት ገበያው የአይምሮ እናት በመባል የሚታወቁት ዶር እሌኒና ከፍተኛ የስራ አስኪያጆች ቡድን በሀገር ውስጥ በሰለጠኑ ባለሙያዎች እንደሚተኩም የምርት ገበያው አስታውቋል።

እስከ ሰኔ 2005 ድረስ ከውጭ የመጣው የስራ አስኪያጅ ቢሮ፤ ስራውን በሽግግር ለሃገር ውስጥ ባለሙያዎች ያስተላልፋል። ዶር እሌኒ ከሃምሌ 25 ጀምሮ ሃላፊነታቸውን ከአቢሲኒያ ባንክ ለተመረጡት አቶ አንተንህ አሰፋ ያስረክባሉ።

አዲሱ የስራ አስኪያጆች ቡድን ከመስራች አስተዳድሩ ጋር በሚቀጥለው ዓመት አብሮ እንደሚሰራም ታውቋል።

የኢትዮጵያ የምርት ገበያ በ2ሽህ ዓም ምህረት የተመሰረተ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠሩ የግብርና ምርቶችን ለገበያ ያቀርባል።

ከዶክተር እሌኒ ገብረ-መድህን ጋር ቪኦኤ ያደረገውን ቃለምልልስ ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG