በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሞያሌው ግጭት 33ሽህ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ኬንያ አሰደደ


የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታው ሁኔታ ስለተሻሻለ ግጭቱን የሸሹት ኢትዮጵያዊያን ወዳገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አስተላልፏል

በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ወረዳ ባለፈው ሳምንት በሶስት ቀበሌዎች የተቀሰቀሰው የጎሳ ግጭት ከ33ሽህ በላይ ሰዎች ወደ ኬንያ ማፈናቀሉን የኬንያ ቀይ-መስቀል አስታወቀ።

በአካባቢው የሚኖሩት የቦረናና የገሬ ጎሳ አባላት ግጭቱ የተጀመረው በጨሙቅ ቀበሌ ሸዎባሬና መለብ ቀበሌዎች ሲሆን በፍጥነት ወደ ወረዳው ከተማ ሞያሌ በመሸጋገር ከ20 በላይ ሰዎችን ማቁሰሉንና መገደሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን እያጣራ ስለሆነ፤ የጉዳቱን መጠን ማወቅ እንዳልቻለ ገልጿል።

በሞያሌ ከተማና አካባቢዋ በኦሮሚያ ክልልና በሶማሊ ክልል የይገባናል ጥያቄ ላለፉት ሃያ አመታት መፍትሄ ያልተበጀለት ጉዳይ ነው። የአሁኑ ግጭት ከግጦሽ መሬትና ከውሃ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

ከአዲስ አበባ ዘጋቢዎቻችን ያነጋገሯቸው ምንጮች በበኩላቸው ከ28 በላይ ሰዎች በያቤሎ ሆስፖታል ቆስለው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። በሞያሌ ጤና ጣቢያ በርካታ የቆሰሉ ሰዎች የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው እንደነበረ፤ ከተለያዩ የአይን ምስክሮች ተረድተናል።

የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ግጭቱ የጎሳ መሆኑን ለዝግጅት ክፍላችን ጠቅሰው፤ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉና እየመረመሩ መሆኑን፤ ለጊዜው ግን ቅድሚያ የሚሰጡን ሰላምና መረጋጋቱን በማስመለስ ላይ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሞያሌ ከተማና አካባቢዋ በኦሮሚያ ክልልና በሶማሊ ክልል የይገባናል ጥያቄ ላለፉት ሃያ አመታት መፍትሄ ያልተበጀለት ጉዳይ ነው። የአሁኑ ግጭት ከግጦሽ መሬትና ከውሃ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

በአካባቢው የሚኖሩት የቦረናና የገሬ ጎሳ አባላት መካከል ባለፈው ሳምንት የበረታ ውጊያ መቀስቀሱን ነዋሪዎችም ባለስልጥናትም ይገልጻሉ።

በዛሬውለት የኢትዮጵያ የመከላከያ ሃይልና የፌዴራል የጸጥታ ሃይሎች ከአካባቢው ታጣቂዎች ጋር በመሆን፤ ግጭቱ ጋብ እንዲል ማድረጋቸውን ምስክሮችም የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናትም ገልጸውልናል።

የዚህን ዘገባ ዝርዝር ያዳምጡ

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG