በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአራት ሰዎችን ህይወት ለቀጠፈው የአርሲ ግጭት ተጠያቂው ማን ነው?


በምእራብ አርሲ አሳሳ ከተማ ለአራት ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆነውን ፖሊስና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል የተቀሰቀሰ ግጭት ሃላፊነት ማን እንደሚወስድ እያወዛገበ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት በሃይማኖት ሽፋን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲመሩ የነበሩ አንድ የአሳሳ ከተማ ነዋሪን የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ሲያውሉ፤ ግብረ አበሮቹ በፈጠሩት ሁከት በሰው ላይና በንብረት ጥፋት ደርሷል ብሏል።

በስፍራው የነበሩ የአይን ምስክሮች ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰው፤ ለምን እንደሚታሰር፤ ከታሰረም መብቱ ተጠብቆ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲያመራ፤ ወይም የአካባቢው ማህበረሰብ ለህግ እንዲያቀርብ በጠይቁ ጊዜ ፖሊሶች ሁኔታውን ባለመቀበል ሰውየውን ሲያስሩ፤ ማህበረሰቡ በቁጣ ድንጋይ መወርወር መጀመሩን ይገልጻሉ። ለዚህ ቁጣ የፖሊስ አጸፋዊ ምላሽ ጥይት በቀጥታ ውደ ሰዎች መተኮስ እንደነበር በስፍራው የነበሩ ሰዎች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል።

ከኦሮሚያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ኮማንደር አበበ ለገሰና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG