በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋዜጠኝነት የሞያ ፍቃድ፥ የንግግርና የፕሬስ ነጻነት ኅጎችና ጥበቃ በዩናይትድ ስቴትስ


የመገናኛ ብዙኃን ተቋሙ ራሱ የጋዜጠኛውን የሞያ ብቃት አረጋግጦ ከሚፈጽመው በስተቀር በዩናይትድ ስቴትስ ጋዜጠኛውን ለሥራው ፍቃድ የሚሰጥና የሚጠይቅ ወገን የለም

ባለፈው ወር በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው የቡድን ስምንት ጉባኤ ወቅት ሥነ ሥርዓቱ በመካሄድ ላይ ሳለ የተፈጠረን አንድ ለየት ያለ ሁኔታ ተከትሎ «ተወሰዱ፤» የተባሉ እርምጃዎችን ትክክለኝነት እንድናረጋግጥ በርካታ አድማጮች የደረሱን ጥያቄዎች ናቸው፤ መነሻችን።

በጉባኤው ከተጋበዙ አራት የአፍሪቃ መሪዎች አንዱ የሆኑት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ንግግራቸውን እንደ ጀመሩ «መለስ ዜናዊ አምባገነን ናቸው፤ የምንፈልገው ከምግብ በፊት ነጻነት ነው።» የሚል ድምጽ በጉባኤው አዳራሽ ለጋዜጠኞች ከተመደበው ሥፍራ ይሰማል።

ድምጹን ከፍ አድርጎ እነኚህን ቃላት ጮሆ በመናገር የጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር ያቋረጠው የኢሳት ጋዜጠኛ አበበ ገላው፥ “በዚህ ድርጊቱ የተነሳ የጋዜጠኝነት ሞያ ፍቃዱን ተነጠቀ? እንዲህ ባሉ በዩናይትድ ስቴትስ መንግስት በሚዘጋጁ መድረኮችም ዳግም እንዳይሳተፍ ታገደ፤” የሚል ዜና አደመጥን። መረጃው ትክክለኛ ነው ወይ?» ሲሉ ቁጥራቸው የበዛ አድማጮች ላደረሱን ጥያቄዎች ምላሽ በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ያለውን መሠረታዊ የጋዜጠኝነት አሠራር አስመልክቶ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተሰናዳ ዝግጅት ነው።

የውይይቱን ሙሉ ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ፤

XS
SM
MD
LG