በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለአብያተ ክርስቲያናቱ ቃጠሎ በመነሻነት የሚሰጡት ምክኒያቶችና ከድርጊቱ ጀርባ አሉ የተባሉ ወገኖች ማንነት ዛሬም እያነጋገረ ነው


ከዋሪጃ ማነው? በቃጠሎውስ ያለው ሚና?

ምዕራብ ኦሮሚያ፥ ጅማ ከተማ አቅራቢያ የምትገኘውን የአሰንዳቦን ከተማ ጨምሮ በአካባቢው ያሉ በርካታ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናትና የግለሰቦችን ቤትና ንብረት የለኮሰው «ከዋሪጃ፤» የተባለው ፅንፈኛ ቡድን ነው፤ ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ባለፈው ሳምንት መገባደጂያ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ለመሆኑ ይሄ «ካዋሪጃ፤» የተሰኘ ቡድን ማነው? በዚህ ቃጠሎ ያለውስ ሚና? ጠቅላይ ሚንስትሩ የመንግስታቸውን ድምዳሜ አስመልክቶ ከፈነጠቁት ፍንጭ ውጪ፥ መንስኤና መላ ፍለጋው በቀጠለበት ጉዳይ ዙሪያ አሁንም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰሙ ነው።
በአዲስ አበባ በእስልምና ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መፅሄት አዘጋጅና በዋሽንግተን ዲሲ የክርስቲያኖች ጉዳይ ተከታታይ ዓለም አቀፍ ድርጅት የአፍሪቃ ጉዳይ ተጠሪ ለአብያተ ክርስቲያናቱ ቃጠሎ በመነሻ ምክኒያትነት በቀረቡ ምክኒያቶች፥ በከዋሪጃ ማንነትና በቃጠሎው አለ በተባለው ሚና ዙሪያ የየበኩላቸውን ይገልፃሉ።

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያድምጡ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG