በቦስተን ዩኒቨርሲቲ የፍሬዴሪክ ፓርዲ የጥናት ማዕከል ለህትመት የበቃውና የኢትዮጵያን ምርጥ ቡና ጅምር ጥረት በምሳሌነት የተመለከተው ይህ ጥናት፥ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ጥበቃ፥ እስካሁን እምብዛም ተጠቃሚ ያላደረጋቸውን አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ደሃ አገሮችንም፤ እንደ ግዙፉ አትራፊ ኩባንያዎች ሁሉ፥ የትሩፋቱ ተቋዳሽ ሊያደርግ የሚያስችል አቅም እንደሚያጎናፅፍ ያመላክታል።
አንድ የምርት ውጤት ቁሳዊ ይዞታው ከሚያስገኛቸው ቀጥተኛ ጠቀሜታዎች ባሻገር፤ ከምርቱን ልዩ መሆን፥ ምንነት፥ ሥምና ዝናው ወይም ዕውቅናው፤ እንዲሁም ምርቱ የፈለቀበትን ባህል የመሳሰሉ ባህሪያቱ የሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች ዋነኞቹ ከአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ዕሴቶች ናቸው።
«ቡና፥ ባህልና የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት፤» የምሽቱ የባህልና ማኅበረሰብ ፕሮግራም እንግዳ፥ የታሪክ አጥኚዋ ዶ/ር ሄራን ሰረቀብርሃን ያተኮሩበት የጥናት ርዕስ ነው።
የጥናታቸውን ይዘትና ምንነት ጨምሮ፥ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነትን የዚህ መንገድ ትርጓሜ፤ እንዲሁም ዘርፉ ሊያስገኝ ይችላል ተብሎ የሚታሰበውን ጠቀሜታ የተመለከቱ ነጥቦች በተከታታይ ቅንብሮች እንመለከታለን።
የመጀመሪያውን ክፍል አጭር ዝግጅት ቀጥሎ ያዳምጡ።