በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዘንድሮው የSEED ተሸላሚዎች አንዱ፤ ዶ/ር ረዳ ተክለሃይማኖት የመልካም ምግባር አረዓያው ሃኪም


(ሦሥተኛ ክፍል)

በህክምና ሊረዳ የሚችል የዓይነ-ሥውርነትና የአካል ጉዳት በሽታዎች ህክምና የሚሰጥ የበጎ አድራጎት ተቋም ነው። መስማት ለተሳናቸው የሚሰጥ የህክምና አገልግሎትና በልጅነት ልምሻ ለአካል ጉዳት ለተዳረጉ ወገኖችም በሚሰጠው አገልግሎት ይታወቃል። «ግራር ቤት ተሃድሶ ማኅበር፤» ይባላል።

ከ15 ዓመታት በፊት ባቋቋሙት በዚህ ተቋማቸው አማካኝነት፥ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የንፁህ ውሃ አቅርቦት ማዳረስን ጨምሮ ቁጥራቸው በበዙ የበጎ አድራጎት አገልግሎቶች የህብረተሰቡን ህይወት ለማሻሻል የያዙት ሥራ ከዘንድሮው
የSEED ማለትም «ማኅበረ ግዩራን ዘረ-ኢትዮጵያ» ተሸላሚዎች አንዱ ለመሆን አብቅቷቸዋል። ዕውቁ የነርቭ ሃኪም ፕሮፌሰር ረዳ ተክለኃይማኖት፤ ዛሬም አብረውን ያመሻሉ።

በቀደሙ ሁለት ፕሮግራሞቻችን እንዳቀረብነው ሁሉ የፕሮፌሰር ረዳን የተወደሰ ሥራ በቅርበት የተከታተሉትንና የድርጅቱን አገልግሎት ተጠቃሚዎች የምስክርነት ቃል ያባሰቡትን አቶ ጴጥሮስ አክሊሉን ጨምሮ ከሁለቱ እንግዶች ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ የመጨረሻ ክፍል ቀጥሎ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG