በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዘንድሮው የSEED ተሸላሚዎች አንዱ፤ ዶ/ር ረዳ ተክለሃይማኖት የመልካም ምግባር አረዓያው ሃኪም


(የመጀመሪያ ክፍል)

የአካል ጉዳት የሚያስከትል ህመም ያደረባቸውን ከማከምና በበሽታቸው ምክኒያት የሚደርስባቸውን መገለል ከማስቀረት ባሻገር ራሳቸውን እንዲችሉ ማብቃት፤ ቁጥራቸው ከበዙ የሥኬት ሥራዎቻቸው ውስጥ ጥቂቱ ናቸው። የንፁህ ውሃ አቅርቦትን ጨምሮ የማኅበረሰቡን ሁለንተናዊ ህይወት እስከ ማሻሻል የደረሱ ክንውኖችን ዕውን አድርገዋል።

በእንግሊዝኛው ምህፃረ ቃል SEED በመባል የሚታወቀውና በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት («ማኅበረ-ግዩራን ዘረ ኢትዮጵያ፤» የአማርኛ ሙሉ ሥያሜው ነው፤) በዘንድሮው 19ኛው ዓመታዊ ሥነ ሥርዓቱ ለሽልማት ካበቃቸው አንዱ ናቸው፤ ዕውቁ የነርቭ ሃኪም ፕሮፌሰር ረዳ ተክለኃይማኖት።

ሥፍራው፥ ቡታጅራ ኢትዮጵያ፤ ድርጅቱ «ግራር ቤት፥ ተሃድሶ ማኅበር፤» ይባላል።

የፕሮፌሰር ረዳን የተወደሰ ሥራ በቅርበት የተከታተሉትንና የድርጅቱን አገልግሎት ተጠቃሚዎች የምስክርነት ቃል በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ያሰሙትን አቶ ጴጥሮስ አክሊሉን ጨምሮ ከሁለቱ ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ ቀጥሎ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG