በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዘንድሮው የSEED ተሸላሚዎች አንዱ፤ ዶ/ር ረዳ ተክለሃይማኖት የመልካም ምግባር አረዓያው ሃኪም


(ሁለተኛ ክፍል)

«ግራር ቤት ተሃድሶ ማኅበር፤» ይባላል።

በህክምና ሊረዳ የሚችል የዓይነ-ሥውርነትና የአካል ጉዳት በሽታዎች ህክምና የሚሰጥ የበጎ አድራጎት ተቋም ነው። መስማት ለተሳናቸው የሚሰጥ የህክምና አገልግሎትና በልጅነት ልምሻ ለአካል ጉዳት ለተዳረጉ ወገኖችም በሚሰጠው አገልግሎት ይታወቃል።

ከ15 ዓመታት በፊት ባቋቋሙት በዚህ ተቋማቸው አማካኝነት፥ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የንፁህ ውሃ አቅርቦት ማዳረስን ጨምሮ ቁጥራቸው በበዙ የበጎ አድራጎት አገልግሎቶች የህብረተሰቡን ህይወት ለማሻሻል የያዙት ሥራ ከዘንድሮው የSEED ማለትም «ማኅበረ ግዩራን ዘረ-ኢትዮጵያ» ተሸላሚዎች አንዱ ለመሆን የበቁት ዕውቁ የነርቭ ሃኪም ፕሮፌሰር ረዳ ተክለኃይማኖት፤ ዛሬም አብረውን ያመሻሉ።

የባህልና ማኅበረሰብ አዘጋጅና አቅራቢ አሉላ ከበደ በምሽቱ ፕሮግራሙ የፕሮፌሰር ረዳን ሥራዎች በቅርበት የተከታተሉትንና ሽልማቱ ያጯቸውን የዋሽንግተን አካባቢ ነዋሪ አቶ ጴጥሮስ አክሊሉን ጨምሮ አወያይቷል።

የውይይቱን ሁለተኛ ክፍል ለምሽቱ እንዲህ ተቀናብሯል።

XS
SM
MD
LG