በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የመላው ኢትዮጵያ የስፖርት ማኅበር ESAONE እና ውዝግቦቹ


«ለማስተዋወቂያ ያወጣነው የገንዘብ ወጪ አነስተኛ ነው። ሂሳቡ ገና ባለመሰላቱ ይሄ ነው የሚባል ቁጥር መናገር ግን አልችልም። ከወገኖቻችን ጋር አብረው የሚኖሩ አፍሪካውያን-አሜሪካውያንና ሌሎች ዜጎችም አንድ ላይ የሚያያዝ ዝግጅት ነው። በሥራችን በጣም ረክተናል።» ESAONE «ገንዘብ በገፍ በማፍሰስ በውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ ለመከፋፈል የተደረገ ያልተሳካ አሳዛኝ ጥረት ነበር። መና ቀርቷል።» የቡድኑ ተቃዋሚዎች።

ሃያ ዘጠኝ ዓመት ካስቆጠረውና ከእርሱ ከቀደመው የሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን የሥራ አመራር በወጡ ግለሰቦች የተቋቋመው አዲሱ ማኅበር እንዴትና ለምን ተመሰረተ?

ዓላማና ውጥኑ፥ የገንዘብ ረጂው ሚድሮክ ኢትዮጵያና ውዝግቦቹ የሚሉትን በተቺዎቹ የሚነሱ ርዕሰ ጉዳዮች በዝርዝር እንመለከታለን።

ከማኅበሩ የቢዝነስ ልማት ዲሬክተር አቶ ብስራት ደስታ ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ፤

XS
SM
MD
LG