በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካዊው ሪቻርድ ኤች ቴሌር በምጣኔ ኃብት ምርምር ዘርፍ የኖቤል ተሸላሚ ሆኑ


ቴለር የተመረጡት “የሰውን ልጅ ጠባይና የምጣኔ ሃብት አስመልክቶ ላበረከቱት የምርምር አስተዋፅዖ ነው”ሲል የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ይፋ አድርጓል።

ቴለር የተመረጡት “የሰውን ልጅ ጠባይና የምጣኔ ሃብት አስመልክቶ ላበረከቱት የምርምር አስተዋፅዖ ነው”ሲል የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ይፋ አድርጓል።

“የምክኒያታዊነትን ውሱንነት፤ የማሕበራዊ ዝንባሌንና ራስን የመግታት አቅም መላላትን ውጤቶች በማጥናትና በመመርመር የሰብዓዊ ማንነታችን እንደምን አድርጎ በረቀቀ መንገድ የሸመታ ውሳኔዎቻችንን እንደሚጫናቸው ቴለር ማሳየት ችለዋል።” ሲል አብራቷል የስዊድኑ የኖቤል አካዳሚ።

የምጣኔ ሃብት ሳይንስ ተመራማሪው “የአእምሮ የሂሳብ አያያዝ” የሚል መጠሪያ የሰጡትንና ሰዎች የውሳኔያቸውን አጠቃላይ ውጤት ከማጤን ይልቅ እያንዳንዱን የገንዘብ አያያዛቸውን የሚመለከት ውሳኔ በተናጠል የሚያይ “የሂሳብ ደብተር” (ማስያ) በአንጎላቸው የሚያበጁበትን አሠራር የሚተነትን ንድፈ ሃሳብ ያፈለቁ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG