በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ሕክምና ቡድን ሾፊር ኢትዮጵያ ውስጥ ተገደለ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት መሠረቱን ያደረገ ትርፋማ ያልሆነ የሕክምና ቡድን ሾፌር ኢትዮጵያ ውስጥ ይጓዝበት የነበረ መኪና ላይ ተኩስ መከፈቱን ተከትሉ ሕይወቱ ማለፉን ድርጅቱ አስታውቋል።

ሙስጠፋ አልኪስሚ የሕክምና ቡድኑ ዓለም አቀፍ ሾፌር ሲሆን፣ ባለፈው ዓርብ ቡድኑ በአማራ ክልል ለሥራ በሚጓዝበት ወቅት በተከፈተ ተኩስ እንደተገደለ የቡድኑ ቃል አቀባይ ኬረን ፒያት ለአሶስዬትድ ፕረስ በኢሜይል አስታውቀዋል። ሌሎች የቡድኑ አባላት ላይም ጉዳት እንደደረሰ ቃል አቀባይዋ ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት ሆን ተብሎ በሠራተኞቹ ላይ ተኩስ ተከፍቶበታል ብሎ እንደማያምን ድርጅቱ አስታውቋል።

በእ.አ.አ 1979 የተመሠረተው ድርጅት ቀውስ በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ይታወቃል።

በሚያዚያ 2013 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሥራውን የጀመረው ድርጅቱ፣ በአምስት ክልሎች ለሚገኙ ፍልሰተኞች፣ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች እንዲሁም የግጭት ሰለባ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጤና አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG