በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኮሪያዋን የድንበር ከተማ አቋርጦ የገባው አሜሪካዊ በፒዮንግያንግ በቁጥጥር ሥር ዋለ


ሁለቱን ኮሪያዎች በሚለዩበት ፓንሙንጆም የደቡብ ኮሪያ ወታደር ቆሞ ይታያል፤ ደቡብ ኮሪያ እአአ የካቲት 7/2023
ሁለቱን ኮሪያዎች በሚለዩበት ፓንሙንጆም የደቡብ ኮሪያ ወታደር ቆሞ ይታያል፤ ደቡብ ኮሪያ እአአ የካቲት 7/2023

የአሜሪካ ዜግነት ያለው አንድ ግለሰብ፣ በዛሬው ዕለት፣ በሕገ ወጥ መንገድ፣ የሰሜን ኮሪያን ድንበር አቋርጦ በመግባቱ፣ በቁጥጥር ሥር ውሏል። ሥፍራው፣ ከወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ነፃ ከኾነው፣ የሁለቱ አገሮች የጋራ ደኅንነት ቀጣና አቅራቢያ እንደሚገኝ ታውቋል።

ከድንበሩ ላይ የሰፈረው፣ የተባበሩት መንግሥታት የሕብረ ብሔር ወታደራዊ ዕዝ፣ ሰውዬው፥ ከወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ነፃ በኾነው የሁለቱ አገሮች የጋራ ደኅንነት ቀጣና፣ አካባቢውን ተዘዋውሮ ለማየት ሲሰናዳ እንደነበር በማረጋገጥ፣ ‘ለድንገቱ እልባት ፍለጋ’ ከሰሜን ኮሪያ ጦር ሰራዊት ጋራ “እየሠራኹ ነው” ብሏል።

የደቡብ ኮሪያው ዕለታዊ ጋዜጣ ዘ ቾሰን ኢልቦ፣ ስማቸው ይፋ ያልተደረጉ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፣ ግለሰቡ፣ ዛሬ ማክሰኞ፣ በአገሬው የሰዓት አቆጣጠር 9፡27 ላይ፣ የሰሜን ኮሪያን ወታደራዊ መስመር ድንገት አቋርጦ ገብቷል።

ይኹንና፣ የሁለቱ ኮሪያዎች ወታደሮች፣ ሌት ተቀን እርስ በርስ እንደተፋጠጡ ዘብ ከሚቆሙበት፤ ከፍተኛ ወታደራዊ ውጥረት ከበዛበት የድንበር ከተማ ድንገት መግባቱን ተከትሎ፣ የተሰማ የተኩስ ልውውጥ ያለመኖሩንም ተመልክቷል።

የደቡብ ኮሪያ ጦር ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት፣ የሰሜን ኮሪያን ድንበር አቋርጦ በፒዩንግያንግ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አባል የኾነ ወታደር ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG