በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በብሪታንያ በሥለት ከተገደሉት አንዱ አሜሪካዊ መሆኑ ተዘገበ


ባሳለፍነው ቅዳሜ ብሪታንያ ሬዲንግ ከተማ ውስጥ በሥለት ከተገደሉት ሦስት ሰዎች መካከል አንዱ አሜሪካዊ መሆኑን በብሪታንያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማንነቱን ሳይገልጹ አረጋገጡ።

አምባሳደር ውዲ ጆንሰን ለጥቃቱ ሰለባዎች ጥልቅ ሃዘናችንን እንገልጻለን፤ ጥቃቱን አጥብቀን እናወግዛለን፤ የብሪታንያን ህግ አስከባሪዎች እንረዳለን ብለዋል።

የብሪታንያ ፖሊሶች እንደገለጡት የሥለት ጥቃቱ በደረሰበት አካባቢ አንድ የሃያ አምስት ዓመት ወጣት የሆነ የከተማዋ ነዋሪ በቁጥጥር ሥር ውሏል፤ ድርጊቱን የፈጸመው ብቻውን ነው ብለው እንደሚያምኑ ጠቁመዋል። ፖሊስም በሽብርተነት ምርመራ እንደከፈተበትም ተገልጿል።

ፊላዴልፊያ ኢንኩዋየረር የተባለው ጋዜጣ፤ የተገደለው አሜሪካዊ ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት ኑሮውን በእንግሊዝ ያደረገ፤ ጆ ሪቺ ቤኔት የተባለ የሠላሳ ዘጠኝ ዓመት ሰው እንደሆነ ዘግበዋል።

XS
SM
MD
LG