በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ታሪክ ዳግም ወደ ዋይት ሃውስ ለመመለስ ዕድል ያገኙት ሁለተኛው ፕሬዝዳንት


ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ
ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ
በዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ታሪክ ዳግም ወደ ዋይት ሃውስ ለመመለስ ዕድል ያገኙት ሁለተኛው ፕሬዝዳንት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:36 0:00

ባለፈው ማከኞው ምርጫ በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን፤ የእንደራሴዎች ምክር ቤቱን ከእጁ ያስገባውን እና እስካሁን በተቆጠረውም ድምጽ የተወካዮች ምክር ቤቱን ውጤት በአብላጫ ድምጽ እየመራ ያለው የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ያሁኑ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የካቢኔ አባሎቻቸውንና ከፍተኛ አማካሪዎቻቸውን ከወዲሁ ይፋ ማድረግ ይዘዋል።

የሕግ መምህና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኙ ዶ/ር ተሻገር ወርቁ
የሕግ መምህና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኙ ዶ/ር ተሻገር ወርቁ

ዳግም ወደ ዋይት ሃውስ የሚመለሱበትን ያልተጠበቀ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙትን የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕን ለዚህ ስኬት ያበቁት ምክኒያቶች የፖለቲካ አዋቂዎችን እና የሌሎችን ትኩረት በተመሳሳይ ስበዋል።

በማናቸውም ሁኔታዎች በሙሉ ልባቸው ትራምፕን በመደገፍ ከሚታወቁት የፓርቲያቸው አጥባቂ ደጋፊዎች፤ ለሁለቱም ፓርቲዎች ወገንተኝነት እስከ ከሌላቸው መራጮች እና ብሎም በዲሞክራት ፓርቲ ደጋፊነታቸው እስከሚታወቁ በርካቶች ድረስ፤ በተመሳሳይ ድምጻቸውን ለትረምፕ ለመስጠት የወሰኑባቸው እነኚህ ሁኔታዎች፤ ያልጠበቁት የገጠማቸውን የተፎካካሪው ፓርቲ ደጋፊዎች ጨምሮ ብዙዎችን ለውይይት መጋበዛቸው አልቀረም። በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የሕግ መምህሩንና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኙን ዶ/ር ተሻገር ወርቁን አነጋግረናል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG