No media source currently available
የአምቦ ከተማ ወደ አንፃራዊ መረጋጋት ተመልሳ መንግዶች መከፈታቸውንና የንግድ እንቅስቃሴ መጀመሩን የከተማው ከንቲባ ገልፁ። ለጠፋው የሰው ህይወትና ለወደመው ንብረት ማዘናቸውን ገልፀው፣ አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የማጣራት ተግባር እየተከናወነ ነው ብለዋል። የአምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል ባለፉት ሁለት ቀናት ግጭት አምስት ሰዎች መሞታቸውንና 20 ሰዎች በህክምና ላይ እንደሚገኙ አረጋግጧል።