No media source currently available
በአምቦ ከተማ ከትናንት ጀምሮ ከ50 በላይ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ታሰሩ ሲሉ አንዳንድ የታሳሪ ቤተሰቦች ተናገሩ። ከታሰሩት ሰዎች መካከል የኦነግ አባላትም እንደሚገኙበት ድርጅቱ አመልክቷል። የአምቦ ከተማ ከንቲባና የአስተዳደር ፅህፈቱ ቤት ኃላፊ በበኩላቸው ሰዎቹ የታሰሩት በሚያራምዱት የፖለቲካ አመለካከት ሳይሆን በወንጀል ድርጊት በመጠረጠራቸው ነው ይላሉ።